ፓስፖርት ለመቀየር /ለማደስ

 ፓስፖርት ለመቀየር በሚቀርብ ጥያቄ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች

                እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ፣

 • የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ ወይም ገጽቹ ያለቁ ፓስፖርት ለመቀየር
 • የቀድሞው ፓስፖርት ከነኮፒው ተያይዞ ሲቀርብ፣

ከ18 አመት በታችለ ሆኑ የፓስፖርት እድሳት ጠያቂዎች

 • የህፃኑ ፓስፖርት ዋናው ከነኮፒው፣
 • ለማስፈፀም የቀረበው አባት ከሆነ የአባት የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም
 • የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ፣
 •  እናት ከሆነች የህፃኑን የልደት ሰርትፍኬት፣የእናት የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት
 • ወይም የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ፣ ማቅረብ ያስፈልጋል።
 • የህጻኑ የፓስፖርት አገልግሎት ጥያቄ ወላጅ መቅረብ ካልቻለ
 • በሞግዚት፣ በተወካይ እና በጉዲፈቻ የቀረበ ከሆነ
 • የሞግዚትነት የውክልና የአሳዳጊነት ወይም ጉዲፈቻ አድራጊነት የተፈቀደበት ማስረጃ አግባብ ካለው
 • መንግስታዊ አካል ማቅረብ ያስፈልጋል።