ለፓስፖርት አገልግሎት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

 ለአዲስ ፓስፖርት ጠያቂዎች

         እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ጠያቂዎች

 • የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም፣
 • አገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ ወይም፣
 • ውጭ አገር ነዋሪ ሆነው በሊሴፓሴ የገቡ ከሆነ ወደ አገር በገቡ በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ሊሴፓሴውን ይዘው በመቅረብና
 • በወሳኝ ኩነት የተመዘገበ የልደት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

እድሜያቸው ከ18 አመት በታች ለሆኑ አዲስ ፓስፖርት ጠያቂዎች

ወላጆች ይዘው ሲቀርቡ ማሟላት ያለባቸው

 • ፓስፖርት ሲጠየቅ ህፃኑ በአካል መቅረብ አለበት፣
 • እድሜው ከ6 ወር በታች ለሆነ ህፃን የሆስፒታል የልደት ማስረጃ በማቅረብ የሚስተናገዱ ሲሆን
 •  ከ6 ወር በላይ ለሆናቸው ህፃናት በወሳኩነቶች የተዘጋጀ የልደት ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
 • መጠኑ ¾ የሆነ የህፃኑ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
 •  የወላጅ የቀበሌ /የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት/፣

 የህጻኑ የፓስፖርት አገልግሎት ጥያቄ ወላጅ መቅረብ ካልቻለ

 •  በሞግዚት፣ በተወካይ እና በጉዲፈቻ የቀረበ ከሆነ
 •  የሞግዚትነት የውክልና የአሳዳጊነት ወይም ጉዲፈቻ አድራጊነት የተፈቀደበት ማስረጃ አግባብ ካለው
 •  መንግስታዊ አካል ማቅረብ ያስፈልጋል።


 በሕጋዊ መንገድ ለሰራ ወደ ውጭ አገር የሚሄድ ማንኛውም ሰራተኛ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማሟላት ይጠበቅበታል፦

 •  ቢያንስ የስምንተኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀ፣
 • በሚቀጠርበት የሥራ መስክ አግባብ ካለው የምዘና ማዕከል (ቴክኒክናሙያ) የሙያ ብቃት ማረጋገጫ
 • ማስረጃ የያዘ፣መሆን አለበት፡፡
 • ዕድሜው ከ21 ዓመት በላይ የሆነ፣
 • የጤና ምርመራ ያደረገ መሆን እንዳአበት ይደነግጋል።

አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቦታዎች

 • አዲስ አበባ ከሚገኘው የዋና መምሪያው ጽሕፈት ቤት በተጨማሪ ከዚህ ቀጥሎ በተገለጹት ቅርንጫፍ ጽህፈትቤቶች አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

1.  ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

2.  ደሴ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

3.  ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

4.  ባህርዳር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

5.  መቐለ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

6.  ጅማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

7.  ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

8.  ሳመራ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

9.  አዳማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

 እንዲሁም በውጭሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ማግኘት

ይችላሉ።


የአገልግሎት ክፍያ

ተ.ቁ

የጉዞሰነድአይነት

የገጽ

ብዛት

በአገር

ውስጥ

በብር

በውጭበሚሲዩንሲሰጥ

በ USD

1

መደበኛፖስፓርት

32

600.00

60.00

2

መደበኛፖስፓርት

64

2186.00

110.00


ለግንዛቤዎ

 •  በተደጋጋሚ ወደ ውጭ የሚመላለሱ በመሆኑ ምክንያት የፓስፖርቶ ገጾች ከፓስፖርቱ የአገልግሎት
 • ጊዜ በፊት ቢያልቅብዎ ባለ 64 ገጽ ፓስፖርት መጠየቅ ይችላሉ።
 • ፓስፖርት በአስቸኳይ ለማግኘት የሚያስገድድ ሁኔታ ቢገጥሞት ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ
 • እንዲሁም በኤጀንሲው ተቀባይነት ያለው ማስረጃዎችን ማቅረብ ይገባል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

 • በጊዜያዊ መታወቂያ አገልግሎት አንሰጥም፣
 • ማንኛውም ባለጉዳይ የሚያቀርበው ሰነድ ህጋዊእና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት፣
 • በተጭበረበረ ሰነድ ለመስተናገድ መሞከር በህግ ያስጠይቃል፡፡