መነሻ ገጽ
አገልግሎቶች
ፓስፖርት
አዲስ ፓስፖርት
ፓስፖርት እድሳት
የጠፋ ወይም የተሰረቀ ፓስፖርት
ፓስፖርት መረጃ መቀየር
ቪዛ
ቱሪስት ቪዛ
ቢዝነስ ቪዛ
ትራንዚት ቪዛ
የተማሪ ቪዛ (am-ET)
የመኖሪያ ፍቃድ
የወሳኝ ኩነት
የልደት ምዝገባ
የሞት ምዝገባ
የጋብቻ ምዝገባ
የፍቺ ምዝገባ
ኦላይን-ኢትዮጲያን ፓስፖርት ሰርቪስ
ኦላይን-ኢትዮጲያን ኢ-ቪዛ ሰርቪስ
ዜና
ማስታወቂያ
የስራ ማስታወቂያወች
የጨረታወች ማስታወቂያወች
አድራሻችን
ታሪክ
ለግንዛቤዎ
Site
Web
Search
Login
You are here:
አገልግሎቶች
የወሳኝ ኩነት
የጋብቻ ምዝገባ
Enter Title
የጋብቻ ምዝገባ
ተጋቢዎች ጋብቻ ለመፈፀም ማሰባቸውን ጋብቻቸውን ለመፈፀም ከወሰኑበት ቀን ከአንድ ወር በፊት ለክብር መዝገብ ሹሙ ማስታወቅ አለባቸው፡፡ ሆኖም ይህ ድንጋጌ በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስርዓት የሚፈፀም ጋብቻን አይመለከትም፡፡
ወንዱም ሆነ ሴቷ በህግ የተፈቀደው የጋብቻ ዕድሜ ሳይደረስ ጋብቻ መፈጸም አይችሉም፡፡ ሆኖም በህግ ስልጣን የተሰጠው አካል ሲፈቀድ የጋብቻ ዕድሜ በህጉ ከተቀመጠው ከሁለት ዓመት ያልበለጠ ጊዜ በመቀነስ ጋብቻውን መፈፀም ይችላል፡፡
ጋብቻ ህግ በሚከለክላቸው የስጋና የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል መፈፀም የተከለከለ ነው፡፡
ተጋቢዎች በፍርድ ቤት እንዳያገቡ የተከለከሉ መሆናቸውን የሚገልጽ የጽሁፍ ማስረጃ የተገኘ እንደሆነ የክብር መዝገብ ሹሙ ጋብቻውን አይመዘገብም፡፡
አንዲት ሴት አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ከቀረ በኃላ አንድ መቶ ሰማኒያ ቀን ማለፉ ካልተረጋገጠ በስተቀር ከሌላ ሰው ጋር ጋብቻ መፈፀም የተከለከለ ነው፡፡ ሆኖም ግን የወለደች እንደሆነ ወይም ከቀድሞ ባሏ ጋር ጋብቻ የምትፈፅም ከሆነ ወይም ነፍሰ-ጡር አለመሆኗ በህክምና ከተረጋገጠ ወይም በብቸኝነት እንዳትኖር ፍርድ ቤት የፈቀደ መሆኑ ሲረጋገጥ ጋብቻው ይመዘገባል፡፡
የሚፀና ጋብቻ ተፈፀመ የሚባለው ተጋቢዎቹ ለመጋባት ነፃና ሙሉ ፈቃዳቸውን ሲሰጡ ብቻ ነው፡፡
ከሁለቱ ተጋቢዎች አንዱ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጋ መሆን ይገባቸዋል፡፡
በሙሽራው በኩል 2 በሙሽሪት በኩል 2 በድምሩ 4 ምስክሮች መቅረብ አለባቸው፡፡
ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎች
በወቅቱ የታደሰ የተጋቢዎች የነዋሪነት/ብሄራዊ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት መቅረብ አለበት፡፡
የተጋቢ ምስክሮች አገልግሎቱ ያላለፈበት የነዋሪነት/ብሄራዊ መታወቂያ መቅረብ አለበት፡፡
ሙሽራው/ዋ ከዚህ በፊት አግብቶ/ታ የፈታ/ች ከሆነ የፍቺ ምስክር ወረቀት መቅረብ አለበት፡፡
አንዲት ሴት አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ከቀረ በኋላ አዲስ ጋብቻ መፈፀም ብትፈልግ አንድ መቶ ሰማኒያ ቀን ሳይሞላ ለማግባት የሚያስችላት ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባት፡፡
ከ 6 ወር ወዲህ በተመሳሳይ ጊዜ የተነሱት ሁለት ሁለት 3 በ 4 የሆነ የተጋቢዎች ፎቶ-ግራፍ መቅረብ አለበት፡፡
በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስርዓት የተፈፀመ ጋብቻ የተጋቢዎች ምስክሮች ወይም በጋብቻ ስርዓቱ ላይ የታደመ ሰው በክብር መዝገብ ሹሙ ፊት በአካል ቀርበው ፊርማቸውን ማኖር አለባቸው፡፡
የተጋቢዎች የልደት ምስክር ወረቀት መቅረብ አለበት፡፡ የልደት ምስክር ወረቀት ከሌላቸው አስቀድሞ ልደታቸዉ መመዝገብ አለበት፡፡
ዘግይተውና የምዝገባ ጊዜውን አሳልፈው ለሚቀርቡ ተመዝጋቢዎች በእስር ወይም በህመም ወይም በመሳሰሉት የቆዩ ከሆነ ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
© 2021 Copyright: Immigration Nationality and Vital Events Agency Ethiopia
Terms Of Use
Privacy Statement